skip to main content

ስለ ዳታው ክስተት ያለው የሕግ ማስታወቂያ

ከኦዲተር McCarthy የተለከ ደብዳቤ (የታደሰው 5/21/2021

Washington State Auditor Pat McCarthy

የዋሽንግተን ግዛት ኦዲተር (“SAO”) ጽ/ቤት ይህንን ድረ-ገጽ ያዘመነው በ SOA ለኦዲት አላማ የሶስተኛ ወገን ከፍተኛ የፋይል ማስተላለፍ አገልግሎት ለተጠቀመው፣ የAccellion የመረጃ ደህንነት ክስተት በ SAO የተወሰደ የዘመነ ምላሽ ለመስጠት ነው።

ስለዚህ ክስተት መጀመሪያ ከተረዳን ጀምሮ፣ SAO ሁለት ዓላማዎች ነበሩት፡(1) የግል መረጃቸው ላይ ተጽዕኖ ደርሶባቸው ሊሆን የሚችሉ ግለሰቦችን ለመርዳት፣ ነጥሎ ማወቅ፣ ማሳወቅ እና ሚረዷቸውን ሀብቶች ማቅረብ፤ እና (2) የግል መረጃዎችን የምናስተላልፍባቸው እና የምንጠብቅባቸው መንገዶች ማሳደግ።


በማርች ወር፣ ከ 2017 እስከ 2020 ባለው ጊዜ ውስጥ ከሥራ አጥነት ክፍያ ጋር በተያያዙ የመረጃ ፋይሎች ውስጥ መረጃዎቻቸው ለሆኑ ሰዎች የኢሜል ማሳወቂያዎችን የመላክ ሂደቱን አጠናቅቀን ነበር። ተጽዕኖ ሊያሳድርብዎት ይችላል ብለው የሚያስቡ ከሆነ፣ ነገር ግን ኢሜሉን ካልተቀበሉ ወይም ኢሜሉ ከሌላቸው፣ ይህ ድረ-ገጽ ለአንድ ዓመት ነፃ የብድር ቁጥጥር እና የማንነት ስርቆት መልሶ የማቋቋም አገልግሎቶችን እንዴት መመዝገብ እንደሚችሉ ጨምሮ ተመሳሳይ መረጃ ይዟል። ተቸማሪ ጥያቄ ካለዎት፣ ወደተሰየመው የጥሪ ማዕከላችን ከሰኞ እስከ አርብ 8:00 AM – 5:00 PM የፓስፊክ ሰዓት አቆጣጠር በ 1-855-789-0673 ይደውሉ።


ቀጣይነ እንዳለው ምርመራችን አካል፣ በቅርቡ ችግሩ በተከሰተበት ወቅት በAccellion መድረክ ላይ የነበሩትን ሌሎች የመረጃ ፋይሎችን የሕግ ምርመራ አጠናቅቀናል። ይህ ግምገማ የግል መረጃዎቻቸው ተጽዕኖ ሊያሳድሩባቸው የሚችሉ ሌሎች ሰዎችን ለመለየት የሚያስፈልገውን መረጃ አቅርቧል። SAO የግለሰቦችን የእውቂያ መረጃ ለማግኘት ወይም ለማረጋገጥ እና ለማሳወቅ መረጃው ከተሳተፈባቸው የግዛት እና የአከባቢ ድርጅቶች ጋር እየሰራ ነው። በእነዚህ ችግር በደረሰባቸው የውሂብ ፋይሎች ውስጥ የማኅበራዊ ዋስትና ቁጥሮች የነበሯቸው ሰዎች ነፃ የአሥራ ሁለት ወር የብድር ቁጥጥር እና የማንነት መልሶ የማቋቋም አገልግሎት ይሰጣቸዋል።


SAO በእነዚህ ችግር በደረሰባቸው የውሂብ ፋይሎች ውስጥ የማኅበራዊ ዋስትና ቁጥሮች የነበሯቸው ሰዎች ነፃ የአሥራ ሁለት ወር የብድር ቁጥጥር እና የማንነት መልሶ የማቋቋም አገልግሎት ይሰጣቸዋል። ይህ ጉዳይ ሊያስከትለው በሚችለው ማናቸውም ጭንቀት ወይም አለመመቸት በጥልቀት ይቅርታ እንጠይቃለን። ምንም አይነት ጥያቄ ካለዎት፣ እባክዎን ወደተሰየመው የጥሪ ማዕከላችን ከሰኞ እስከ አርብ 8:00 AM – 5:00 PM የፓስፊክ ሰዓት አቆጣጠር በ 1-855789-0673 ለመደወል አያመንቱ። በተጨማሪም, በዚህ ድህረ ገጽ ላይ, sao.wa.gov/breach2021, ሁልጊዜ አዳዲስ መረጃዎችን እንለቃለን።

ከሠላምታ ጋር ፣

Pat McCarthy

የዋሽንግተን ግዛት ኦዲተር

ስለ መረጃ መመዝበር በተደጋጋሚ የሚነሱ ጥያቄዎች

ምን ተፈጠረ? በጥር 2021 አጋማሽ፣ የ Accellion ፋይል የማስተላለፍ አገልግሎትን ሊያካትት ከሚችል የፀጥታ ችግር ጋር ተያይዞ ነበር ። SAO ለተለየ ዝርዝር መረጃ ወዲያውኑ Accellion ን አነጋግሯል። በሚቀጥሉት ጥቂት ሳምንታት ውስጥ SAO ያልተፈቀደለት ሰው በ SAO ፋይል ማስተላለፍ መለያ ውስጥ ከ Accellion ጋር የተከማቸውን ውሂብ መዳረሻ ማግኘቱን ተረድቷል። SAO የተከሰተውን ስፋት እና ለSAO የኦዲት ዓላማ በተላከው መረጃ ላይ ምን ያህል ተጽዕኖ ሊያሳድር እንደሚችል ለማወቅ ወዲያውኑ ምርመራውን የጀመረ ሲሆን፣ በአደጋው በየትኞቹ ፋይሎች ላይ ተጽዕኖ እንደደረሰ ለመለየት ከAccellion ጋር ሰርቷል። SAO እንዲሁ ምርመራው ላይ እንዲረዱ የሳይበር ደህንነት ባለሙያዎችን አሳት።

ምን መረጃ ተካቷል? ከ 2017 እስከ 2020 ባለው ጊዜ ውስጥ በሥራ ስምሪት ደህንነት መምሪያ ከከፈሉት የሥራ አጥነት ጥቅሞች ጋር በተያያዘ መረጃዎቻቸው በመረጃ ፋይሎች ውስጥ ለነበሩ ሰዎች ማሳወቂያዎች በኢሜል ተልከው ነበር። እነዚህ ፋይሎች ምናልባትም የሰዉዬውን ስም፣ የማህበራዊ ደህንነት ቁጥር(የሶሻል ሴኪዩሪቲ ቁጥር)፣ የትውልድ ቀን፣ የመኖሪያ ቤቱ ዋና ጎዳና እና የኢሜል አድራሻ፣ እና/ወይም የባንክ ሂሳብ ቁጥር እና የባንክ ማዘዋወሪያ ቁጥር በውስጣቸው ልሂዙ ይችላሉ።

SAO እንዲሁም የAccellion አደጋ ደርሶባቸው ለሚችሉ ሌሎች የክልል ኤጀንሲዎች እና የአከባቢ መንግስታት የውሂብ ፋይሎች ውስጥ በህግ ምርመራ መረጃቸው ለታወቀ ሰዎች የግል ማሳወቂያዎችን እየላከ ነው። እነዚህ ፋይሎች ከሚከተሉት ውስጥ ሁሉንም ሳይሆን አንዱ ወይም ከዚያ በላይ ነበራቸው፡ የሰዎች ስሞች፣ የማኅበራዊ ዋስትና ቁጥሮች፣ የተማሪ መለያ ቁጥሮች፣ የትውልድ ቀን፣ የብድር ወይም የባንክ ሂሳብ ቁጥሮች፣ የጤና መድን ቁጥሮች እና/ወይም ከጤና ጋር የተዛመዱ መረጃዎች።

የወሽንግተን ነዋሪዎች ዒላማ ተደርገዋል? ይህ ክስተት በአለም ዙሪያ በሚገኙ የAccellion ደንበኞችን የጎዳ ሲሆን በአሁኑ ወቅት በህግ አስከባሪዎች ምርመራ እየተደረገበት ይገኛል። የዋሽንግተን ግዛት ወይም ማናቸውም ነዋሪዎቹ የዚህ ክስተት ዒላማ እንደነበሩ የሚያሳይ እስከዛሬ ድረስ ምንም ማስረጃ የለም። ይህ ክስተት በርካታ የፌደራል እና የክልል፣ የአከባቢ፣ የጎሳ እና የግዛት መንግስታዊ ድርጅቶች እንዲሁም የኢንዱስትሪ ድርጅቶችና በሕክምና ንግዶች፣ በሕግ፣ በቴሌኮሙኒኬሽን፣ በፋይናንስ፣ በከፍተኛ ትምህርት፣ በችርቻሮ እና በሃይል ዘርፎች ያሉትን ጨምሮ የግል ኢንዱስትሪ ድርጅቶች ንግድ ላይ ተጽኖ አሳድሯል።

SAO ያረጀ ወይም ጊዜው ያለፈበት ምርትን እየተጠቀመ ነበር? ጥሰቱ በተፈፀመበት ጊዜ፣ Accellion SAO እና ሌሎች ብዙ ድርጅቶች ሲጠቀሙበት የነበረውን የፋይል ማስተላለፊያ ስርዓትን እየደገፈ እና እያገለገለ ነበር። በ 2020 መጨረሻ፣ SAO ወደ Accellion አዲሱ የመሣሪያ ስርዓት፣ Kiteworks የማዘዋወር ሂደት ጀመረ፣ ይህም በታህሳስ 31, 2020 ተጠናቀቀ

የማህበራዊ ዋስትና ቁጥርዎ የነበረበት ከሆነ ነፃ የብድር ቁጥጥር እና ሌሎች አገልግሎቶችን እንዴት ማግኘት እንደሚቻል (የዘመነው 5/21/2021)

በ Accellion ክስተት ውስጥ የማኅበራዊ ዋስትና ቁጥራቸው የተጋለጡ ሊሆኑ ለሚችሉ ሰዎች በExperian በኩል ለሚገኘው SAO ለ 12 ወራት ነፃ የብድር ቁጥጥር እና የማንነት መልሶ የማቋቋም አገልግሎቶችን እያደረገ ነው። በግላዊነት ህጎች ምክንያት በቀጥታ ልንመዘግብዎት አልቻልንም።


በExperian ለብድር ቁጥጥር ለመመዝገብ አክቲቬሽን ኮድ ከተለዩ መመሪያዎች ጋር ማሳወቂያ ከደረስዎት እባክዎ በዚያ ማሳወቂያ ውስጥ ያሉትን መመሪያዎች ይከተሉ። የማኅበራዊ ዋስትና ቁጥርዎ በAccellion አደጋው ውስጥ ስለመኖሩ እርግጠኛ ካልሆኑ፣ ወይም SAO የላከልዎትን የግንኙነት አድራሻ ማግኘት ካልቻሉ፣ እባክዎን ለታታሪ የጥሪ ማዕከላችን በ 1-855-789-0673 ይደውሉ፣ ከሰኞ – አርብ ከ 8:00 a.m. – 5:00 p.m. እናም ለነፃ የብድር ቁጥጥር ብቁ መሆን አለመሆንዎን ለማወቅ ተወካይ ሊረዱዎት ይችላሉ።


ፕሮግራሙ ሁለት ነገሮች በውስጡ ይዟል፦
የብድር ቁጥጥር። ለኤክስፔሪያኖች የማንነት ስራዎች ክሬዲት 3B ነጻ የ 12 ወር አባልነት። ይህ ምርት ሦስቱን ዋናዋና የብድር ወኪሎች በመከታተል የግል መረጃዎን ያለአግባብ መጠቀምን ለመለየት ይረዳል እንዲሁም የማንነት ስርቆትን ወዲያውኑ በመለየት እና በመፍታት ላይ ያተኮሩ የማንነት ጥበቃ አገልግሎቶችን ይሰጥዎታል። የማንነት ስራዎች ክሬዲት 3B ለእርስዎ ሙሉ በሙሉ ነፃ ነው እናም በዚህ ፕሮግራም ውስጥ መመዝገብ የብድር ውጤትዎን አይጎዳውም።


ማንነትን መመለስ መረጃዎን ወይም የማንነት ስርቆትዎን በተጭበረበረ መንገድ መጠቀሙን ከተጠራጠሩ እና እነዚያን ጉዳዮች እንዴት መፍታት እንደሚቻል ለመወያየት ከፈለጉ ፣ ከዚህ በታች ለExperian የእውቂያ መረጃውን በመጠቀም የExperian ወኪልን ማግኘት ይችላሉ። ይህ አገልግሎት ለአንድ ዓመት ያህል ለእርስዎ ይገኛል እና በዚህ ጊዜ እንዲመዘገቡ ወይም ሌላ ማንኛውንም እርምጃ እንዲወስዱ አይፈልግም። ሁኔታዎን ከወኪል ጋር ከተወያዩ በኋላ ከሆነ ፣የማንነት መልሶ ማቋቋም ድጋፍ እንደሚያስፈልግ ተወስኗል ፣ችግሩ ከተከሰተበት ቀን ጀምሮ የተከሰተውን እያንዳንዱን የማጭበርበር ወንጀል (እንደአስፈላጊነቱ ፣ክሶችን ለመከራከር እና ሂሳቦችን ለመዝጋት አበዳሪዎችን በማነጋገር እርስዎን በማገዝ; ከሶስት ዋና የብድር ቢሮዎች ጋር በብድር ፋይልዎን እንዲያግዱ እርስዎን ማገዝ; እና ማንነትዎን ወደነበረበት እንዲመልሱ ከመንግስት ኤጄንሲዎች ጋር በመገናኘት እርስዎን መርዳትን ጨምሮ) ለመመርመር እና ለመፍታት ከእርስዎ ጋር አብሮ ለመስራት የ Experian ማንነት መልሶ ማቋቋም ወኪል ይገኛል።


ግላዊ የሆነ የማስጀመሪያ ኮድ(አክቲቬሽን ኮድ) ከ SAO ግንኙነት ከተቀበሉ፡ ከ የዋሽንግተን ስቴት ኦዲተር አደጋ ምላሽ ሰጪ አካል በተቀበለው ኢሜል ውስጥ የቀረበውን የግል የምዝገባ ማስጀመሪያ ኮድዎን በመጠቀም በ ኤክስፔሪያን በኩል ለ 12 ወራት ነፃ የብድር ቁጥጥር/ማንነት መልሶ የማቋቋም ፕሮግራም መመዝገብ ይችላሉ። ለበለጠ መረጃ www.experianidworks.com/3bcredit ን ይጎብኙ።


ግላዊ በሆነው ያማስጀመሪያ ኮድዎ፣ ከዚህ በታች ያለውን ነጻ የስልክ መስመር በመጠቀም በቀጥታ ለኤክስፔሪያን መደወል ይችላሉ: 1-833-256-3154. ተወካዮቹ እርስዎን ለመርዳት እና ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 6:00 እስከ 8:00 ድረስ ስለ ፕሮግራሙ ለሚነሱ ጥያቄዎች መልስ ለመስጠት ዝግጁ ናቸው። PST እና ቅዳሜ/እሁድ 8:00a.m.-5:00p.m. PST.

ከ 2017 እስከ 2020 ባለው ጊዜ ውስጥ የሥራ እጥነት ጥቅሞችን ከተቀበሉ፣ ነገር ግን ግላዊ የሆነ አክቲቬሽን ኮድ በማርች 15 ቀን 2021 በኢሜል ካልተቀበሉ፣ የምዝገባው ጊዜ እስከ ጁን 6 ቀን 2021 ክፍት ይሆናል። እነዚህን መመሪያዎች በመከተል አሁንም በExperian የብድር ቁጥጥር ውስጥ መመዝገብ ይችላሉ፡

  1. በፕሮግራሙ ውስጥ ለመመዝገብ www.experianidworks.com/3bcredit ን ይጎብኙ ወይም ከክፍያ ነፃ ቁጥርን በመጠቀም በቀጥታ ወደ ኤክስፕሪያ ይደውሉ: 1-833-256-3154፣
  2. ኮዱን ማቅረብ ያስፈልግዎታል: WSHAUD2021.
  3. የተሳትፎ ቁጥሩን ማስገባት ያስፈልግዎታል: B009702
  4. ምዝገባው ክፍት የሚሆነው እስከ 6/6/2021ነው።

የእርስዎን የ 12-ወር የኤክስፔሪያን ሥራዎችዎ ክሬዲት 3B አባልነትን በተመለከተ ተጨማሪ ዝርዝሮች፡
ለኤክስፔሪያን ማንነት ሥራዎች ክሬዲት 3B ለመመዝገብ የክሬዲት ካርድ አያስፈልግም ።
መመዝገብ ሳያስፈልግ—ማንኛውንም የማጭበርበር ጉዳዮችን በተመለከተ—ወዲያውኑ ባለሙያውን ማነጋገር ይችላሉ። የማንነትን መመለሻ ባለሞያዎች በብድር እና ብድር-ነክ ባልሆኑ ማጭበርበሮች እርስዎን ለመርዳት ዝግጁ ናቸው።
አንዴ በባለሙያ ማንነት ስራዎች ውስጥ ከተመዘገቡ በኋላ ፣ የሚከተሉትን ተጨማሪ ነገሮች ማግኘት ይችላሉ፦

  • በምዝገባ ወቅት የ ኤክስፔሪያን የብድር ሪፖርት፦ ከእርስዎ የብድር ፋይል ጋር ምን ዓይነት መረጃ እንደተያያዘ ይመልከቱ። ዕለታዊ የብድር ሪፖርቶች ለኦንላይን አባላት ብቻ ይገኛሉ።*
  • የብድር ቁጥጥር፦ የማጭበርበር አመልካቾችን የ Experian ፣ Equifax እና የ TransUnion ፋይሎችን በንቃት ይከታተላል።
  • የኤክስፔሪያን የማንነት ሥራዎች ExtendCARETM: የኤክስፔሪያን የማንነት ሥራዎች አባልነትዎ ካለፈ በኋላም ቢሆን ተመሳሳይ የከፍተኛ ደረጃ የማንነት መመለሻ ድጋፍን ይቀበላሉ።
  • የ $1 ሚሊዮን ዳላር የማንነት ስርቆት ኢንሹራንስ**:– ለተወሰኑ ወጪዎች እና ያልተፈቀደ የኤሌክትሮኒክ ገንዘብ ማስተላለፍ ሽፋን ይሰጣል።

* ከመስመር ውጭ የሆኑ አባላት ከተመዘገቡ በኋላ ለተጨማሪ የሩብ ዓመቱ ሪፖርቶች ጥሪ ብቁ ይሆናሉ።
** የማንነት ስርቆት መድን በፅሑፍ ተጽፏል እናም የሚተዳደረው በአሜሪካ የባንኮች ኢንሹራንስ ኩባንያ ፍሎሪዳ የተባለ የኢንሹራንስ ኩባንያ ነው። ለሽያጭ ውሎች ፣ ሁኔታዎች እና የሽፋን ማግለል እባክዎ ትክክለኛውን ፖሊሲዎች ይመልከቱ። ሽፋን በሁሉም ግዛቶች ውስጥ ላይገኝ ይችላል።

ከማንነት ስርቆት እራስን ለመጠበቅ መለማመድ ያሉብን ጥሩ ነገሮች

የአካዎንትዎን መግለጫዎች ይከልሱ እና አጠራጣሪ እንቅስቃሴን ለህግ አስከባሪ አካላት ያሳውቁ: እንደ የጥንቃቄ እርምጃ እርስዎ ንቁ ሆነው እንዲቆዩ እና የሂሳብ መግለጫዎችን እና የብድር ሪፖርቶችን በቅርብ እንዲመለከቱ እንመክራለን። በመለያው ላይ ማንኛውንም አጠራጣሪ እንቅስቃሴ ካዩ ወዲያውኑ ሂሳቡ ለተያዘለት የገንዘብ ተቋም ወይም ኩባንያ ማሳወቅ አለብዎት. እንዲሁም ማንኛውንም የማጭበርበር ድርጊት ወይም የተጠረጠሩ የማንነት ስርቆት ክስተቶች በትክክል ለህግ አስከባሪ ባለሥልጣናት ፣ ለክልል ጠቅላይ አቃቤ ህግዎ እና ለ / ወይም ለፌዴራል ንግድ ኮሚሽን (“Federal Trade Commission, FTC)” ማሳወቅ አለብዎት።

የብድር ሪፖርት ቅጅ: www.annualcreditreport.com/ ን በመጎብኘት በየ 12 ወሩ አንድ ጊዜ ከእያንዳንዱ ሶስት ዋና ዋና የብድር ሪፖርት ወኪሎች ነፃ የብድር ሪፖርትዎን ቅጅ ማግኘት፣በ ነጻ የ ስልክ ቁጥር 877-322-8228 በመደወል፣ ወይም ዓመታዊ የብድር ሪፖርት መጠየቂያ ቅጽ በመሙላት ወደ ዓመታዊ የብድር ሪፖርት አገልግሎት በፖስታ በመላክ ይችላሉ፣ የፖ.ሳ. ቁጥር 105281, Atlanta, GA 30348. እንዲሁም ከሚከተሉት ሶስት ብሔራዊ የብድር ሪፖርት ወኪሎች ጋር መገናኘት ይችላሉ:

Equifax
P.O. Box 105851
Atlanta፤ GA 30348
1-800-525-6285
www.equifax.com

Experian
P.O. Box 9532
Allen፤ TX 75013
1-888-397-3742
www.experian.com

TransUnion
P.O. Box 1000
Chester፣ PA 19016
1-877-322-8228
www.transunion.com

የማጭበርበር ማስጠንቀቂያ: በብድር ሪፖርትዎ ላይ የማጭበርበር ማስጠንቀቂያ ለማስቀመጥ ሊፈልጉ ይችላሉ። የመጀመሪያ የማጭበርበር ማስጠንቀቂያ ነፃ ሲሆን በብድር ፋይልዎ ላይ ለአንድ ዓመት ይቆያል። ማስጠንቀቂያው በሪፖርትዎ ውስጥ ሊኖር ስለሚችል የማጭበርበር ተግባር ለአበዳሪዎች ያሳውቃል እንዲሁም አበዳሪው በስምዎ ውስጥ ማንኛውንም ሂሳብ ከማቋቋምዎ በፊት እንዲያገኝዎት ይጠይቃል። በዱቤ ሪፖርትዎ ላይ የማጭበርበር ማስጠንቀቂያ ለማስቀመጥ ከዚህ በላይ ከተጠቀሱት ከሦስቱ የብድር ሪፖርት ወኪሎች ጋር ይገናኙ። ተጨማሪ መረጃ በ www.annualcreditreport.com.ላይ ይገኛል።

የደህንነት እቀባ (Security Freeze): በዋሽንግተን ግዛት እና በሌሎች አንዳንድ ግዛቶች ውስጥ በብድር ፋይልዎ ላይ የደህንነት እገዳ የማድረግ መብት አለዎት። ይህ እቀባውን ሲጀምሩ ለእርስዎ የተሰጠውን PIN ሳይጠቀም በስምዎ አዲስ ብድር እንዳይከፈት ይከላከላል። የደህንነት እቀባው ያለእርስዎ ፈቃድ አበዳሪ ሊሆኑ የሚችሉ የብድር ዝግባዎን እንዳያገኙ ለመከላከል የተቀየሰ ነው። በዚህ ምክንያት የደህንነት እገዳን በመጠቀም ብድር የማግኘት ችሎታዎን ሊያደናቅፍ ወይም ሊያዘገይ ይችላል። ከእያንዳንዱ የብድር ሪፖርት ወኪል ጋር በብድር ፋይልዎ ላይ የደህንነት እቀባውን ለየብቻ ማስቀመጥ አለብዎት። የደህንነት እቀባውን ለማስቀመጥ ፣ ለማንሳት ወይም ለማስወገድ ምንም ክፍያ የለም። የደህንነት እቀባውን ለማኖር፣ ሙሉ ስምዎን፣ የሶሻል ሴኩሪቲ(Social security) ቁጥርዎን ፣ የትውልድ ቀንዎን ፣ የአሁኑን እና የቀድሞ አድራሻዎትን ፣ በክፍለ-ግዛት የተሰጠዎትን የመታወቂያ ካርድ ቅጂ ጨምሮ ለሸማቾች ሪፖርት ኤጀንሲ እርስዎ መሆኑን የሚለይ መረጃ፣እና የቅርብ ጊዜ የፍጆታ ሂሳብ ፣ የባንክ ሂሳብ መግለጫ ወይም የኢንሹራንስ መግለጫ እንዲያቀርቡ ሊጠየቁ ይችላሉ።

ተጨማሪ ነፃ ሀብቶች: የማንነት ስርቆትን ለመከላከል ስለሚወስዷቸው እርምጃዎች ከሸማቾች ሪፖርት ኤጀንሲዎች ፣ ከፌዴራል ንግድ ኮሚሽን ወይም ከክልል ጠቅላይ አቃቤ ህግ መረጃ ማግኘት ይችላሉ። የተጠረጠሩ የማንነት ስርቆትን ለአከባቢው የሕግ አስከባሪ አካላት ሪፖርት ማድረግ ይችላሉ ፣ለ FTC ወይም የክልል ጠቅላይ አቃቤ ህግን ጨምሮ። የ FTC(የፌዴራል ንግድ ኮሚሽን) የእውቅያ መረጃ እዚህ ይገኛል፡

የፌዴራል ንግድ ኮሚሽን, 600 Pennsylvania Ave, NW, Washington, DC 20580 www.consumer.ftc.gov, and www.ftc.gov/idtheft
1-877-438-4338

በ በፍትሃዊ የብድር ሪፖርት ሕግ(Fair Credit Reporting Act, FCRA) መሠረትም የተወሰኑ መብቶች አሉዎት፡ እነዚህ መብቶች በመዝገብዎ ውስጥ ያለውን ማወቅን ፤የተሳሳተ ፣ ያልተሟላ ወይም ሊረጋገጥ የማይችል መረጃን እንዲያስተካክሉ ወይም እንዲሰርዙ የሸማቾች ሪፖርት ወኪሎች መጠየቅ ያካትታሉ። ስለ FCRA የበለጠ መረጃ ለማግኘት, እባክዎን www.consumer.ftc.gov/articles/pdf-0096-fair-credit-reporting-act.pdf.ን ይጎብኙ.

የክስተቱ የጊዜ ሰሌዳ

ጥር. 12፦ SAO ከአሁን በኋላ ካልተጠቀመበት የ Accellion ፋይል ማስተላለፍ መሳሪያ ጋር ሊኖር ስለሚችል የደኅንነት ሁኔታን በተመለከተ SAO ለ Kiteworks የመሳሪያ ስርዓት ተጠቃሚዎች ከ Accellion አጠቃላይ ማስጠንቀቂያ ደርሶታል።
ጥር. 13፦ ወደ SAO በሚላክበትት ወይም በሚመጡበት ጊዜ የትኞቹ ፋይሎች እንደተጎዱ ለማወቅ SAO ለ WaTech አሳውቆ ከ Accellion ጋር ሰፋ ያለ ግንኙነት ላይ ተሰማራ።
የጥር 25 ሳምንት፦ በ Accellion በተገለጹት የተጎዱ የSAO ፋይሎች ውስጥ የተወሰኑት መረጃዎች ከቅጥር ደህንነት መምሪያ (“Employment Security Department, ESD”) የሥራ አጥነት ጥቅሞችን የተቀበሉ ሰዎችን የግል መረጃ እንደ ያዙ ወስኗል።
የካቲት 1፦ SAO ክስተቱን ለህዝብ ይፋ አደረገ። SAO በሕጉ መሠረት የተቀመጡትን ተተኪ የማሳወቂያ አሠራሮችን ተከትሏል እናም ይህንን ክስተት አስመልክቶ ቅድመ ማሳሰቢያ በ SAO ዌብሳይት ላይ በ sao.wa.gov/breach2021 ተለጥፏል፣ይህም እኛ እሻሽለን ያስቀመጥነው ነው።
የካቲት. 12፦ ጠቅላይ አቃቤ ህጉን አሳወቀ። ያ ማስታወቂያ የካቲት 26 የተሟላ ነው።
የካቲት. 25፦ በሥራ አጥነት ጥቅሞች የውሂብ ፋይል ውስጥ ለነበሩ ከክስተቱ ጋር የተዛመደ እገዛን ስለማግኘት እና ኢሜሎችን ስለመላክ SAO ሰዎች ጥያቄ የሚጠይቁበት እና መረጃን የሚያገኙበት የጥሪ ማዕከል አቋቋመ።